top of page
በዘረኘነት የተጎዱን ሰሚ ማዕከል
ስለማእከሉ

በዘረኝነት የተጎዱን ስለሚሰማ ማዕከል

ክፋት እንደ ዶፍ-ዝናብ ሲጥል፣
ማንም የለም "ይቁም!" የሚል፣ 
ወንጀል እየበዛ ሲከመር ሲቆለል፣
ግራ እያጋባ ማየትም ይሳናል። 
ልማድ ሆኖ ሲቀር ስቃይን መታገስ፣
አልሰማ እያለ ጩኸት ባገር ሲነግስ፣ 
እንደበጋ ዝናብ ድምጽ ወደቀ ሳይደርስ።

"ክፋት እንደዶፍ ዝናብ ሲመጣ" ከሚለው የቤርቶልድ ብሬክት ግጥም የተወሰደ

ሰውን በነጠላም ሆነ በቡድን፦ በዘር ምንጭ፣ በሃይማኖት፣ በብሔር ወይም በቆዳው ቀለም ምክንያት በላዩ አሉታዊ አመለካከት፣ ማጥቃትና ልዩነት መፍጠር ከዘረኝነት የሚመነጭ አመለካከት ነው። የእስራኤል ሕግ ዘረኝነትን የሚተረጉመው የተወሰነ ሕዝብን ወይም ከፊሉን ሕዝብ እንደ፦ "ማሳደድ፣ ማዋረድ፣ ማሳፈር፣ ጠላትነት ማሳየት፣ መገዳደር ወይም ማጥቃት ወይም ሽኩቻ መፍጠር ነው"፣ እና ይህ ሁሉ በቀለም ወይም በዘር ምንጭ ወይም የተወሰነ ብሔር-ጎሳ በመሆን የሚከሰት ነው።
በእስራኤል ያለው ዘረኝነት ብዙ ምልክ አለው፦ በማሳደም ሊገለጽ ይችላል - በግራፊክ ሥዕል ወይም እንደማስታወቂያ፤ በሥራ ቦታ ወይም በደንበኝነት ላይ ልዩነት በመፍጠር፤ እና አንዳንድ ጊዜ ጥቃት እስከማድረስ እና እስከግድያ በሚደርስ መገለጫ ሊፈጸም ይችላል። እስራኤል የተለያዩ ማኅበረሰቦችን ያካተተች ሀገር ስትሆን ብዙ አናሳ ብሔረሰቦች በዘረኝነት ምክንያት ይሰቃያሉ። ዐረቦች፣ ከኢትዮጵያ የመጡ አዲስ ገቢዎች፣ ራሺያኛ ተናጋሪዎች፣ ምሥራቃውያን እና መጠለያ ጠያቂ አፍሪካውያን እንደዚሁም ሥራ ፈላጊዎች በልዩነት ላይ የተመሠረተ እኩልነት አልባ እንቅፋት ያጋጥማቸዋል፣ ከፊሎቹም ለጥቃት በመጋለጥ የአካልና የአዕምሮ ጉዳት ይደርስባቸዋል።
ሕጉ ለዘረኝነት ተጎጂዎች ምላሽ ይሰጣል። የዘረኝነት ተጎጂዎች ማዕከል በእነዚህ የዘረኝነት ወንጀሎች ተጎጂ ለሆኑ ሴቶች እና ወንዶች እርዳታ ለማድረግ፣ ህጋዊ ይሆነውን መብታቸውን ለማስገኘት እና እንደአስፈላጊነቱ የሕግ እና የስነልቡና እርዳታ እንዲያገኙ ለማድረግ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ዘረኝነትን ሙሉ ለሙሉ ለመዋጋት ይቻለን ዘንድ የተጎዳችሁበትን ዘረኝነት መጠን እና መልክ ለመረዳት እንጠይቃለን። መረጃዎችን ማሰባሰብና ሪፖርት ማድረግ ዓመታዊ የክትትሎች ሪፖርት ለማዘጋጀት ይጠቅማል። ማዕከሉ ከዘረኝነት ተጎጂዎችም ሆነ ከዘረኝነት ክስተቶች የዓይን ምስክሮች ሪፖርት ለመቀበል ዝግጁ ከመሆኑም በላይ ሪፖርቶችን በዕብራይስጥ፣ በዐረብኛ፣ በራሺያኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ይቀበላል።
ማዕከሉ የተቋቋመው በሃይማኖትና ሀገር ተሐድሶ/ሪፎርም ማዕከል እና በእስራኤል ሀገር ዘረኝነትን ታጋይ ዋና መሥሪያ ቤት ነው።

የመሠረቱት አካላት

የመሠረቱት አካላት

የሃይማኖትና ሀገር ተሐድሶ

የሃይማኖትና ሀገር ተሐድሶ/ሪፎርም ማዕከል በእስራኤል ሀገር የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሕዝባዊ-ሕግ ክንድ ሲሆን ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ ዲሞክራሲን ከማራመድ እና አናሳ ብሔረሰቦችን ከእስራኤል ኅብረተሰብ ጋር ከማዋሃድ ዓላማ ጎን፤ የፕሉራሊዝምን፣ የእኩልነትን እና የሃይማኖት ነጻነትን እሴት ለማስቀደም የሚንቀሳቀስ ነው። ዘረኝነትን መዋጋት ከድርጅቱ መሠረታዊ ተልዕኮዎች አንዱ ነው።
የተሐድሶው ማዕከል በእስራኤል ሀገር የተለያዩ ሃይማኖቶችን ለማራመድ እና የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር ግዴታ ገብቷል። በፍትህና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አጠቃላይ እና ሁሉን አቀፍ የእስራኤል ዲሞክራሲን ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ነው።
የተሐድሶው ማዕከል ተፅዕኖ ለመፍጠር በሚፈልግባቸው ጉዳዮች ላይ፣ ከሕዝብ መመሪያዎች እና ድንጋጌዎች ማራመድ ጎን ዓላማው በሕዝብ አስተያየት ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮ ሕዝብን በቀጥታ ከሚያንቀሳቅስ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ጋር፣ በሕግ መሣሪያዎች ይጠቀማል።

ዘረኝነትን ተሟጋች የሆነው/የሚታገለው ዋና መሥሪያ 

ዘረኝነትን ተሟጋች የሆነው/የሚታገለው ዋና መሥሪያ ቤት ከ45 በላይ የሚሆኑ በቡድኖች ላይ ወይም በግለሰቦች ላይ የሚደረግን በአጠቃላይ፦ በአረብ ወንዶች እና ሴቶች ላይ፣ በኢትዮጵያ ወንዶችና ሴቶች ላይ፣ በምሥራቃውያን ወንዶችና ሴቶች ላይ፣ በራሽያኛ ተናጋሪ ወንዶችና ሴቶች ላይ፣ በሥራ ፈላጊ ስደተኛ ወንዶችና ሴቶች ላይ፣ በመጠለያ ፈላጊ ስደተኞች ሴቶች እና ወንዶች ላይ እና በጾታ ላይ ያነጣጠረ ዘረኝነትንና መድሎን የሚታገሉ ድርጅቶችን፣ ቡድኖችን፣ የእቅስቃሴ ተሳታፊ ወንዶች እና ሴቶችን ያካተተ ጥላ ድርጅት ነው። ዋና መሥሪያ ቤቱ የሚንቀሳቀሰው ከዘረኝነት ነጻ የሆነ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ማኅበረሰብን ራእይ ለማራመድ ነው።
የዋና መሥሪያ ቤቱ አባል ድርጅቶች፦ የሃይማኖትና ሀገር ተሐድሶ/ሪፎርም ማዕከል፣ የ"ትሙራ" ማዕከል፣ በእስራኤል ለሚኖሩ ዐረቦች ድርጅቶች መብት የቆመው የ"ሙሳዋ" ማዕከል፣ የ"ሲኩይ" ማኅበር፣ "ሃኬሼት ሃዲሞክራቲት ሃሚዝራሂት" (የምስራቅ የዲሞክራሲ ቀስተ-ዳመና)፣ "አሆቲ" እንቅስቃሴ፣ የ"ሃካራ"/የማወቅ ፎረም- በኔጌቭ ያሉ ያልታወቁ የበደዊ መንደሮችን ለማወቅ የሚያግዝ፣ የሰላም የሴቶች ኩዋሌሽን/ኅብረት፣ "ማአጋሊም-ሃላካአት"፣ የሰው መብት ሐኪሞች፣ ጠበቃ-ለኢትዮጵያ አዲስ ገቢዎች ሕግ እና ፍትህ፣ "አጀንዳ"፣ "ካቭ ለኦቬድ"፣ ለዜጎች መብት "አብሮ የመኖር ፎረም በኔጌቭ"፣ "ማህፓኽ ታዒር" ጄዳር ማኅበር፣ "ታንዳይ"፣ "ማዓአን"፣ "ሂራክ"፣ "ማሕሶም ዋች"፣ ለተፈናቃዮችና ለስደተኞች፣ የዐረቦችን ትምህርት የሚከታተል ኮሚቴ፣ "የአራድ ቀስተዳመና"፣ "አርባት" የአብርሃም ፈንድ ራእዮች፣ የስብጥር ቤተሰቦች ማኅበር፣ "ሙርሻቴኑ"፣ ሳይኮ-አክቲቭ፣ የሙያ ጥራት ዝርዝር/መዝገብ እና የሰው መብት- በጠበቆች ዋና መሥሪያ ቤት፣ የSOS ማዕከል ለጥቃት ትምህርት በእስራኤል፣ ዘረኝነት በሀገሬ አይደለም ድርጅት፣ የሰላም ትምህርት ቤት በንቬ ሻሎም፣ "ሒራኮና"፣ "አ.ሳ.ፍ" ለተፈናቃዮች እና ለመጠለያ ጠያቂዎች የሚያግዝ ድርጅት፣ "ሚርሐቪም"፣ የእስራኤል ልጆች፣ "ሻቲል"፣ "ኦሲም ሻሎም"፣ የዒአላም ማዕከል፣ የአዶም ሐዳሽ እንቅስቃሴ፣ በራሺያ እና በሶቬት ኅብረት ዩኒቨርሲቲዎች ተምረው ያጠናቀቁ ሰዎች ማኅበር፣ ለዜጎች እኩልነት እና ዘረኝነትን ለመታገል የገሊላ ፎረም፣ የታማራ መሠማሪያ ቤት ማኅበር፣ ከቲራ የአንቲማና የዔአታአ ድርጅት፣ ለእኩልነት እና ዘረኝነትን ለመታገል የደቡብ እና የሻሮን የሦስትዮሽ ፎረም።

የማዕከሉ የሥራ ባልደረቦች

የማዕከሉ የሥራ ባልደረቦች

ጻሒ ምዙማን

ጻሒ ምዙማን 

የሥራ መሪ

የይዘት አዘጋጅ። "ዴኦት" ሼል "ንኤማኔ ቶራ ቨአቮዳ" የሚባለውን መጽሔት ያቋቋመና ያዘጋጅ የነበረ፣ ብዙ እውቅና አካዳሚክ ጽሑፎችን እርማትና ዝግጅት ያደረገ። በ"ማኾን ሶልድ" የአሥራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናዎች ማዕከል የትርጉም ክፍል የሥራ መሪ ሆኖ ከመሥራቱ ባሻገር የ"ታልሙድ" እና የ"ቶሽባ/የቃል ኦሪት" ፈተናዎች ዝግጅት አስተባባሪ ሆኖ አገልግሏል። ከዚህ ቀደም ብሎ በሃይማኖት እና በሀገር ተሐድሶ ማዕከል በነበረው የሥራ ድርሻው የሕዝባዊ አገልግሎት ክፍል የሥራ ኃላፊ ሆኖ ሰርቷል። 

የሌዝቢዎች፣ ጌዮች፣ ሁለት-ወሲብ እና ጾታቸውን የለወጡ (LGBT) ሰዎች መብት እንቅስቃሴ ተሳታፊ፣ እንደዚሁም በሃይማኖተኛው ማኅበረሰብ ውስጥ የሌዝቢዎች፣ ጌዮች፣ ሁለት-ወሲብ እና ጾታቸውን የለወጡ ሰዎችን በተመለከተ መቻቻል እንዲኖር ለማስተማር የሚንቀሳቀሰውን "ሽቫል" የሚባለውን ድርጅት ካቋቋሙ ሰዎችም አንዱ ነው።

በሃይማኖቶች መካከል መግባባትን ለመፍጠር የተመሠረተው "አጎዳ ለሐቫና ቤይን ዳቲት" የሚባለው ማኅበር ሊቀመንበር እና የእንቅስቃሴ ተሳታፊም ሆኖ ሠርቷል።

የሕግ ጠበቃ ናዳል ዖትማን

የሕግ ጠበቃ ናዳል ዖትማን

ተባባሪ የሥራ መሪ፣ የዘረኝነትን ተሟጋች ዋና መሥሪያ ቤት የሥራ መሪ

በ"ሙሳዋ" ድርጅት ማኅበራትን በማደራጀት ሥራው ሥር የዘረኝነትን ተሟጋች ዋና መሥሪያ ቤት ያቋቋመ።

በመገናኛ ብዙሃን (ከ2006-2008) የ"ዶንያ አል-ራያ እና ሻባብ" ሳምንታዊ ጋዜጣ አሳታሚ ሆኖ የሠራ ሲሆን እንደዚሁም በHALAL TV ጣቢያ ብዙ ለሰው መብት ተከራካሪ እና የእንቅስቃሴ ተሳታፊዎችን የጋበዘበት "ሃዝኹት ሼላኑ/መብታችን" የሚባል ፕሮግራም አቅርቧል።

የአስተያየት ጽሑፎችን በአረብኛ እና በዕብራይስጥ ቋንቋ በተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎች ስለሰው ልጆች መብቶች እና ስለእንቅስቃሴ ተሳትፎ ይጽፋል። በአረቦች ማኅበረሰብ ውስጥ ለማኅበራዊ ለውጥ ለሚደራጁ፣ ለፕሮጄክቶችን ለማስፋፋት እና መኅበራዊ ድርጅቶችን ለማቋቋምና ለማጠናከር ምክር ይሰጣል።

የሕግ ጠበቃ ኡሪ ናሮቭ

የሕግ ጠበቃ ኡሪ ናሮቭ 

የሕግ አማካሪ

ራማት ጋን በሚገኘው የሕግና የንግድ አካዳሚ ማዕከል የተማረ። ከቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው። በእስራኤል የአዲስ ገቦች እርዳታ ማኅበረ-ሰብ (HIAS) ፕሮግራም ውስጥ አባል ነው። እንደዚሁም ከ2010 ጀምሮ በእስራኤል የጠበቆች ማኅበር ዋና መሥሪያ ቤት አባል ነው።

ሁሉድ መሳአልሃ 

ሁሉድ መሳአልሃ 

ቃል አቀባይ

የዘረኝነትን ተሟጋች ዋና መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ። ጋዜጠኛና የሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊ። ከሒብሩ ዩኒቨርሲቲ በመገናኛ ብዙሃንና በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር በብዙሃን መገናኛ መስክ ብዙ ኮርሶችን አድርጋለች።

በእስራኤል አረቦች ላይ በተለያዩ ጉዳዮችና መስኮች ስላሉት ተግዳሮቶችና እንቅፋቶች "ትዑዶት አዱሞት/ቀያዮቹ መታወቂያዎች" የሚል ተከታታይ የቴሌቪዢን ተውኔት አዘጋጅታለች።

ምራም ስሊማን

ምራም ስሊማን

በዐረብኛና በዕብራይስጥ ለሚሰጠው አገልግሎት አስተባባሪ/ኮኦርዲኔተር

በዘረኝነት ተሟጋች ዋና መምሪያ የእንቅስቃሴ አስተባባሪ

የኢንተርኔት ድረ-ገጾች ፕሮግራሚንግ የተማረች እና በፕሮግራሚንግ ልምድ ያላት

የደካማ ማኅበረሰብ ልጆችን ለመርዳት በሚደረገው የበጋ እንቅስቃሴ ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ትሳተፋለች።

ያና ቤይሊን

ያና ቤይሊን

በራሺያኛ ቋንቋ ለሚሰጠው አገልግሎት አስተባባሪ/ኮኦርዲኔተር

የዩክሬይን ተወላጅ፣ በቻርኬሲ ከተማ የተሐድሶ መኅበረሰብ ሊቀመንበር ሆና አገልግላለች። በ"ሶህኑት ሃይሁዲት" የጎልማሶች ትምህርት ቤት ዕብራይስጥ ያስተማረች ሲሆን በከተማዋ ዮም ሪእሾን በሚባለው ት/ቤት አስተርምራለች።

ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ የተሐድሶ እንቅስቃሴ በሆነው "መርካዝ ህሲዩዓ ሃሚሽፓቲ ለዖሊም" ("ለአዲስ ገቢዎች የሕግ ዕርዳታ ማዕከል") ሥር የአመልካቾች አስተባባሪ በመሆን ለአዲስ ገቢዎች ዕርዳታ በማድረግ ላይ ትገኛለች።

ኢሳይያስ ሐዋዝ 

ኢሳይያስ ሐዋዝ 

በአማርኛ ቋንቋ ለሚሰጠው አገልግሎት አስተባባሪ/ኮኦርዲኔተር

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ትምህርት ከተማረ በኋላ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲያስተምር ቆይቶ በ1996 መጨረሻ ላይ ወደ እስራኤል ሀገር ገባ። በእስራኤል ሀገር የማሻሻያና "ሪትሬኒንግ" ትምህርት ተምሮ፣ ለ11 ዓመታት በትምህርት ሚኒስቴር በመምህርነት አገልግሏል።

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጤና ትምህርት ክፍል ለሦስት ዓመታት ያህል ሠርቷል።

 

በዚህ ወቅት በሂንሪታ ሶልድ የምርምር ኢኒስቲቲዩት ከትምህርት ጋር የተገናኘ ሥራ ይሠራል። 

እንደዚሁም የትርጉምና የእርማት/ኢዲቲንግ ሥራዎችን ይሠራል።

በእስራኤል ሀገር የማኅበረሰብን ደረጃ ልዩነት ለማጥበብ በሚሠራ"ሲንጉር ክሂላቲ" በሚባል በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በበጎፈቃደኝነት ለሁለት ዓመታት ያህል አገልግሏል።

bottom of page